በአሁኑ ሰዓት ማስታወቂያ መንገድ ላይ መለጠፍ በጣም እየተለመደ መጥቷል፡፡ ማስታወቂያጰች መንገድ ላይ መለጠፋቸው ለማህበረሰቡ መረጃዎችን ለማግኘት በጣም ይረዳቸዋል፤ ምክንያቱም የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ይረዳቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አካባቢዉ ላይ ምን ምን እንዳለ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን አይቶ መረዳት ወይም መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሰለዚህ ማስታወቂያዎችን በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ጊዜ ተጨባጭ መረጃ መውሰድ ይኖርብናል፡፡
መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያወች አብዛኛው በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ጊዜ ጥራቱን የጠበቀ አይደለም፡፡ መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች የሚለጠፉት በስልክ እንጨት እና በመብራት እንጨት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በጣም ጥራት ይጎለዋል እና ደግሞ ፁሑፍዎቹ በጣም የዠጠጋጉ ናቸው፡፡ ሰለዚህ ማህበረሰቡ በቀላሉ ሊረዳው ወይም ሊገነዘበው ይከብዳቸዋል፡፡
መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ብዙ ጊዜ በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ወቅት ሙሉ መረጃን አይሰጡም መንድነዉ ሀሳባቸው በጣም የተወሳሰበ እና የተቆራረጠ ሀሳብ ነዉ፡፡ ብዙ ጊዜ መንገድ ላይ የሚለጠፉ ወይም የሚሰቀሉ ማስታወቂያዎች ሲበጠሱ ወይም ሲነቀሉ የሚያነሳቸው የባለቤት አካል የላቸውም፡፡ ሰለዚህ እነዚህን ማስታወቂያ ማህበረሰቡ መረጃዎችን የማግኘቱ ነገር በጣጡ እየቀነሰ ይመጣል ማለት ነው፡፡
ሰለዚህ መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያ ህብረተሰቡ ባገናዘበ መልኩ መጻፍ አለበት፡፡ ማስታወቂያዎች ብዙ ጊዜ የሚፃፉት በውጭ ሀገር ቋንቋ ነው ነገር ግን መሆን ያለበት ማህበረሰቡ በሚረዳዉ ቋንቋ መሆን አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንገድ ላይ የሚለጠፉ ወይም የሚሰቀሉ ማስታወቂያዎች ባለቤት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በተገነጠሉ ጊዜ ቶሎ በመድረስ ማስተካከል ይኖርበታል የ በለድርሻ አካላት፡፡ በሌላ በኩል መንገድ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ህግና ስርዓቱ የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ