ረቡዕ 18 ሜይ 2016

የአክስ ዶድራንት ማስታወቂያ ምን ይመስላል?




አክስ ዶድራንት ማራኪ እና ጠንከር ያለ ሽታ ያለው መአዛን የሚያላብስ ለየት ያለ እና ሁሌም የሚታወስ ለስለስ ያለ ደንቅ መዓዛ ያዘለ ነው።ጥሩ መዓዛ ሁሌም ቢሆን በሰዎች አእምሮ ውስጥ እንዲታወሱ የሚያደርግ ትልቅ ኃይል አለው።አንገታችን ጀረባ ዶዶራንቱን መጠቀም ጥሩ ቢሆንም በፊታችን.ላይ ማርከፍከፍ ግን ተገቢ አይደለም።አክስ ዶዶራንት ለሰውነታችን እንጂ ለፊታችን የተዘጋጀ አይደለም። አክስ ዶድራንት ለሰዉነታችን ጥሩ መአዛ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የአክስ ዶድራንት ማስታወቂያ በምናይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከሌሎች ከምናያቸዉ ማስታወቂያወች በጣም ለየት ያለ ነዉ፡፡ ማስታወቂያዉ ብዙዉን ጊዜ በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ወቅት ምንም አይነት የድምጽ ንግግር የለውም፤ ይሄን ደግሞ ከሌሎች ከሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ለየት ያደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ማስታወቂያዉ ለማስተላለፍ የሚጠቀምበት ጊዜ በጣም ዉስንና በጣም አጭር ጊዜ ነዉ ሚወስደዉ፡፡
 


የአክስ ዶድራንት በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ወቅት ማስታወቂያዉ መጀመሪያ ሚመጣዉ ወንድልጅና እንደገና አክስ ዶድራንቱ ነው፤ ከዛ በሁአላ ደግሞ ወንድየው በሁለት ሴቶች መካከል ይከበባል ይሄን የሚያሳየው የ አክስ ዶድራንት ምን ያህል መአዛዉ ከፍተኛ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ነገር ግን ማስታወቂያው ላይ ሁለቱም ፆታዎች አያካትትም በሌላ በኩል ደግሞ ማስታወቂያው በሚተላለፍበት ወቅት ድምጽ ሊኖረው ይገባል፡፡ ማስታወቂያዉ ወደ ማህበረሰቡ በሚደርስበት ወቅት ላይረዱት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ማስታወቂያዉ በሚተላለፍበት ወቅት ጉዳቱን አይናገርም በያንስ እንኳን የት የቱጋ እነደሚነፋና እና ማይነፋበት ቦታ አይናገርም፡፡
በአሁኑ ወቅት የአክስ ዶድራንት ማህበረሰቡ በጣም ተጠቃሚ እያደገ ነዉ፡ አክስ የዶድራንት ማስታወቂያ መተላለፍ ያለበት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚረዳዉ መልክ መሆን አለበት፡፡ አሁን ማስታወቂያዉ በምናይበት ወይም በምንመለከትበት ወቅት መንም ኣይነት ድምጽ የለውም ነገር ግን ህብረተሰቡ በቀላሉ እንዲረዳዉ ማስታወቂያዉ በድምፅ መተላለፍ አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዶድራንቱን የት የት በታ እንደምንጠቀምና ዶድራንቱን የማንጠቀምበት የሰዉነት አካላችን ላይ ለይቶ ማስቀመጥ ወይንም መናገር አለበት፤ ምክንያቱም ህብረተሰቡ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ